
ሀገራት ልማትን በማረጋገጥ አዳጊና ተለዋዋጭ የሆነውን ፍላጎት ማሟላትና ኢኮኖሚያቸው በማይናወጥ መሰረት ላይ እንዲመሰረትና በቀጣይ ብልጽግናን እያረጋገጠ እንዲሄድ ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ይህን ውጤት ለማስመዝገብ የዕድገት አቅሞችን በማሰባሰብ መረባረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ሀገራት በራሳቸው ነባራዊ ሁኔታ አቅም አሰባስበው ያደጉበት መንገድ የተለያየ ቢሆንም በኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ውስጥ የግሉ ዘርፍ፣ መንግሥት እና የተለያዩ አደረጃጀቶች ተሳትፎ እና አሻራ በጉልህ ይታያል፡፡ በተከተሉትና በሚያቀነቅኑት የኢኮኖሚ ፖሊሲ መሰረት በማድረግ የእያንዳንዱ ዘርፍ አስተዋጽኦ እና የተሳትፎ ደረጃ የተለያየ ቢሆንም በየትኛውም ሀገር መንግሥት ጣልቃ ገብነት ሳይኖር በገበያ ብቻ ዕድገት ማግኘት እንደማይቻል የታወቀ ነው፡፡ በዚህ መሰረት በሀገራችን ነባራዊ ሁኔታ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ቁልፍ የልማት እና የኢኮኖሚ አንቀሳቃሽ ኃይል ሆነው ቆይተዋል፡፡
ከዚህ ረገድ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር በሀገር ደረጃ የነበሩ የኢኮኖሚ ስብራቶችን ለመጠገን፣ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ እና የግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ ለሀገር የሚያበረክተው ሚና እንዲጎለብት ለማድረግ የተዘጋጀውን ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች እንዲታገዝ የማድረግ ሚናን እየተጫወተ ይገኛል፡፡
የአስተዳደሩ ራዕይም የልማት ድርጅቶችን በዓለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ በማስቻል ለባለድርሻ አካላት ዘላቂነት ያለው እሴትን መፍጠር ሲሆን፣ ይህ በዋናነት በልማት ድርጅቶች ያለን የመንግሥትንና የህዝብን ሀብት ለተሻለ የሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ማዋልን የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ ጋር በተገናኘ አስተዳደሩ ሀገራዊ ተልዕኮውን ለማሳካት በመቋቋሚያ ደንቡ የተሰጡትን አምስት ዋና ዋና ዓላማዎች እንዲተገብር የሚያስችሉ የረዥም ጊዜና የአጭር ጊዜ ስትራቴጂያዊ ዕቅዶችን ቀርጾ እየሰራ ሲሆን፣ በዚህ ተግባር ህልውናቸው ስጋት ላይ ወድቆ የነበሩ የልማት ድርጅቶች ወደ ትርፋማነት እንዲመጡ ተደርጓል፡፡ ወደ ትርፋማነት ከመምጣት ባለፈም በአሁኑ ሰዓት ሌሎች ሀገራዊ ተቋማትን በመደገፍ እና ከብር 1.5 ትሪሊዮን በላይ ሀብትን በማንቀሳቀስ በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ የማይናቅ ሚናን እየተጫወቱ ይገኛል፡፡
በአሁኑ ወቅት መንግሥት በሀገር ኢኮኖሚ ላይ ያጋጠመውን ስብራቶች ለመጠገን የሀገር በቀል ኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀግብር አዘጋጅቶ እየተገበረ ይገኛል፡፡ ከኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀግብሩ ምሶሰሶዎች ውስጥ የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ሪፎርም አንዱ ነው፡፡ በዚህ መሰረት ከ2011 ዓ.ም ጀምሮ ሀገራዊ ለውጥን እና ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመቃኘት በመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር እንዲሁም በመንግሥት የልማት ድርጅቶች የለውጥ ትግበራ መካሔድ ጀምሯል፡፡
ይህ ለውጥ ከሀገራዊ የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ፣ ከመዋቅራዊ ማሻሻያ እና ከፐብሊክ ፋይናንስ አንጻር ከመንግሥት የልማት ድርጅቶች የሚጠበቅን ተግባር ከግምት ውስጥ ያስገባ እና የኢኮኖሚ ማሻሻያ መርሀግብሩን ሊደግፍ የሚችል ነው፡፡ በዚህ መሰረትም ዓለም አቀፍ ተሞክሮዎችን በመዳሰስ የትኩረት መስኮች ተለይተው ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል፡፡ የትኩረት መስኮቹ የልማት ድርጅቶችን ውጤታማና ተወዳዳሪ ከማድረግ፣ የድርጅት አመራር ውጤታማ እንዲሆን ከማስቻል፣ ተቋማዊ አቅምን ከመገንባት፣ ትራንስፎርሜሽንን ከመደገፍና ከማሳለጥ እና በልማት ድርጅቶች የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ሥርዓቶችን ተግባራዊ ከማድረግ አንጻር ያተኮሩ ናቸው፡፡
የልማት ድርጅቶችን ተወዳዳሪ ለማድረግ ስልጣንን፣ ኃላፊነትና ተጠያቂነትን፣ ውሳኔ አሰጣጥን የገንዘብ ምንጭን፣ የካፒታል መዋቅርን፣ የሂሳብ አያያዝ እና ኢንቨስትመንትን የተመለከቱ ጉዳዮች ላይ ትኩረት ሰጥቶ መስራት ይጠበቃል፡፡ በሌላ አገላለጽ ዘመናዊ የአሰራር ሥርዓትን ተግባረዊ ማድረግን ግድ ይላል፡፡ እነዚህን ጉዳዮች ለመመለስ የኮርፖሬት ገቨርናንስና ፋይናንስ ሥርዓቶች ተግባራዊ እየተደረጉ ይገኛል፡፡
አስተዳደሩ ጠንካራ የድርጅት አመራር መርሆዎችንና የአመራር ልምዶችን ተከትሎ፣ ፈጠራ በታከለበት አሰራር የልማት ድርጅቶች ዓለምአቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑና የሀገርን ኢኮኖሚ ከዚህ በተሻለ መልኩ እንዲደግፉ ለማድረግ እየሰራ ቢሆንም ይህ ተግባር የበለጠ ስኬታማ እንዲሆን የባለድርሻ አካላት ንቁ ተሳትፎ፣ ድጋፍና ትብብር ወሳኝ ሚናን እንደሚጫወት ይታመናል፡፡
ይህንን ቁልፍ ተግባር ለማከናወንም የልማት ድርጅቶችን አቅም መገንባት፣ ዓለማአቀፍ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ እና በሀገር ኢኮኖሚ ግንባታ ያላቸው አስተዋጽኦ ደግሞ ከፍ እንዲል የማስቻል አቅጣጫዎች ትኩረት ተሰጥቷቸው የሀገራዊ ብልጽና ጉዞውን የመደገፍ ተግባራት ሲከናወኑ ቆይተዋል፤አሁንም በመከናወን ላይ ናቸው፡፡
በመሆኑም የመንግሥት የልማት ድርጅቶችን ውጤታማና ተወዳዳሪ በማድረግ የሀገርን ኢኮኖሚ እንዲደግፉ ለማስቻልና የሀገር በቀል የኢኮኖሚው ማሻሻያ ዋና ግብ የሆነውን የኢኮኖሚ ስብራት የመጠገን ፣ምርትና ምርታማነትን የማሻሻል እና የግሉን ኢኮኖሚ ተሳትፎ የማሳደግ ዕቅድን በማሳካት ወሳኝ የሀገር ብልጽግና ጉዞን በጋራ ለማሳካት የባለድርሻ አካላት ከአስተዳደሩና ከልማት ድርጅቶች ጎን በመሆን በባለቤትነት መንፈስ እንድትሰሩ ጥሪዮን ለማቅረብ እወዳለሁ፡፡
በጋራ የበለጸገች ሀገርን ለመጭው ትውልድ እናስተላልፋለን!
አመሰግናለሁ!
አቶ ዝናቡ ይርጋ
ተወካይ ዋና ዳይሬክተር
ህዳር 17, 2017
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ተጠሪ ከሆኑ የልማት ድርጅቶች መካከል አንዱ እና በእንስሳት ክትባት ማምረት ዘርፍ በኢትዮጵያና በአፍሪካ ደረጃ ግንባር ቀደም የሆነው የብሔራዊ እንስሳት ጤና ጥበቃ ኢንስቲትዩት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ህዳር 17 ቀን 2017 ዓ.ም ተገመገመ፡፡
ህዳር 16, 2017
ለአስተዳደሩ ተጠሪ ከሆኑ አስር የልማት ድርጅቶች መካከል የዕዳና ሀብት አስተዳደር ኮርፖሬሽን እና የኢንዱስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም ተገመገመ፡፡
ህዳር 13, 2017
በህዳር 13 ቀን 2017 ዓ.ም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን እና የኢትዮጵያ ምድር ባቡር ኮርፖሬሽንን የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ገመገመ፡፡
ህዳር 12 ቀን 2017
የኢትዮጵያ ልማት ባንክና የኢትዮጵያ ፖስታ አገልግሎት ድርጅት የ2017 በጀት ዓመት የመጀመሪያ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ሐሙስ ህዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ከፍተኛ አመራሮች፣ የድርጅቶቹ የቦርድና ማኔጅመንት አባላት ፣ከገንዘብ ሚኒስቴር የሚመለከታቸው የሥራ ኃላፊዎች እና በአስተዳደሩ ተቋማቱን የሚከታተሉ የሥራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በተገኙበት ተገመገመ፡፡
ሀምሌ 6, 2016
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር ከአፍሪካ አመራር ልህቀት አካዳሚ ጋር ሐምሌ 6 ቀን 2016 ዓ.ም በአስተዳደሩ መሰብሰቢያ አዳራሽ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራረመ፡፡
ነሀሴ 16, 2016
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር የኢትዮጵያ መብራት ኃይልን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ሐሙስ ፣ነሐሴ 16 ቀን ፣ 2016 ዓ.ም በኃይሌ ግራንድ ሆቴል መሰብሰቢያ አዳራሽ ተገመገመ፡፡
PEHA ዘርፈ ብዙ አገልግሎቶች ይሰጣል።
EELPA
ብሔራዊ የእንስሳት ሕክምና ተቋም
የኢትዮጵያ ባቡር ኮርፖሬሽን
የኢትዮጵያ ፖስታ
LAMC
ኢትዮ ምህንድስና ቡድን
EIIDE
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ
IPDC
የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ይዞታና አስተዳደር
PEHA
ገርጂ ኢምፔሪያል፣ አዲስ አበባ
Mon – Fri: 8:30 am – 5:30 pm